በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አይዞን ፋውንዴሽን” የሚያበረታቸው የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች


“አይዞን ፋውንዴሽን” የሚያበረታቸው የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:20 0:00

“አይዞን ፋውንዴሽን” የሚያበረታቸው የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች

በጉራጌ ዞን የሚገኘው ወርበኬ የመጀመሪያ ደርጃ ት/ቤት፣ በአሁኑ ወቅት፣ ከ400 በላይ ተማሪዎችን ይዞ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ ኾኖም፣ የመማሪያ ክፍሎቹ በቂ ቁጥር እና ጥራት የሌላቸው በመኾናቸው፣ የአካባቢው ተማሪዎች ርቀው ወደሚገኙ ት/ቤቶች ለቅቀው በመሔድ ላይ እንዳሉ፣ የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር አቶ ረቢክ ሶፊዩ ይናገራሉ። በአሁን ሰዓትም የትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ ያሉትን የመማሪያ ክፍሎች ይዞታ በማሻሻልና ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባት ላይ ትኩረት አድርጎ ከሚንቀሳቀሰው፣ አይዞን ፋውንዴሽን ጋራ አብሮ እየሠራ ይገኛል።

አይዞን ፋውንዴሽን፣ ግብረ ሠናይ ተቋም ሲኾን፣ በኢትዮጵያ በተለይም በገጠራማ ክፍሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሉባቸውን የግንባታ ችግሮች በመገንዘብ፣ የተሻለ ይዞታ ያላቸው የመማሪያ ክፍሎችንና መጸዳጃ ቤቶችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በት/ቤቶች ውስጥ፥ ጠባብ እና ጨለማ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተጨናነቁ የክፍል ወንበሮች፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ የመጸዳጃ ቤቶች፣ እንዲሁም በቂ የንጹሕ ውኃ አቅርቦት አለመኖር፤ በተማሪዎች የትምህርት አቀባበል ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ፋውንዴሽኑ፣ ከመማሪያ ክፍሎች ግንባታ ጎን ለጎን፤ የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ፣ የንጹሕ ውኃ እና የመጸዳጃ ቤቶች አቅርቦት እንዲኖር ይጥራል። የተቋሙ አብዛኛው ሥራ የሚተገበረው፣ በወጣት በጎ ፈቃደኞች አማካይነት ሲኾን፣ ከ190 በላይ የተመዘገቡ በጎ ፍቃደኞች እንዳሉት፣ የተቋሙ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሻሎም ያዕቆብ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

/ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG