በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ፍልሚያው ቀጥሏል 


ሱዳን
ሱዳን

የሱዳን ጦር ኃይል፣ በሱዳን መዲና ካርቱም በስተሰሜን በሆስፒታል አቅራቢያ የሚገኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን ከአየር ደብድቧል። የአይን እማኞች እንደሚሉት ሆስፒታሉ በአየር ጥቃቱ ጉዳት ደርሶበታል።

ግጭቱን ለማቆም እና የሰብአዊ 'ርዳታ ለማድረስ ይቻል ዘንድ በሁለቱ ወገኖች መካከል በጅዳ ሳዑዲ አረቢያ ውይይት በሚደረግበት በዚህ ወቅትም፤ በካርቱም፣ ባህሬን እና ኦምዱርማን ከተሞች ውጊያው ተፋፍሞ ቀጥሏል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ጀኔራል አምዳን ዳጋሎ በውጊያ ላይ ተጎድተዋል ወይም ተገድለዋል የሚለውን ወሬ፣ ኃይሉ በለቀቀው አንድ የድምጽ መልዕክት፤ ጀኔራሉ እራሳቸው አስተባብለዋል።

አንድ ወር ባለፈው ግጭት 200 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገራት ሲሸሹ፣ ከ 700 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በአገር ውስጥ ተፈናቃይ ሆነዋል፡፡ ከ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን እንዳጡ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG