በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የጄነራል አል-ቡርሃንን መልዕክት ተቀበሉ


ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የጄነራል አል-ቡርሃንን መልዕክት ተቀበሉ
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የጄነራል አል-ቡርሃንን መልዕክት ተቀበሉ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሱዳን ላዕላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጄነራል አብዱል-ፈታህ አል-ቡርሃን የተላከ መልዕክት መቀበላቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ዛሬ ባወጡት ትዊት አስታወቁ።

መልክዕክቱን ያደረሱት የጄነራል አል-ቡርሃን ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዳፋላህ አልሃጅ ናቸው።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከአምባሳደሩ ጋር ባደረጉት ውይይት ሱዳንን አሁን ካለችበት ሁኔታ ለማውጣት ጎረቤት ሃገሮችና የምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ልማት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ሊጫወቱ ስለሚችሉት ሚና መነጋገራቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር በትዊታቸው ላይ ጠቁመዋል።

ተኩስ ማቆም እጅግ አስፈላጊ መሆኑንና አጣዳፊ እርምጃ ሊሆን እንደሚገባው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ማሳሰባቸውንና የሱዳን ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት በሱዳናዊያን በራሳቸው ብቻ መሆኑን መናገራቸውን አቶ የማነ አመልክተዋል።

የኢጋድ ሚናም ቢሆን ድጋፍ በመስጠትና በማመቻቸት ላይ የተወሰነ መሆን እንደሚገባው ፕሬዚዳንቱ መጠቆማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትዊት ተናግሯል።

XS
SM
MD
LG