በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ ጎርፍ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺሕ ሊያልፍ ይችላል ተባለ


የሶማሊያ ጎርፍ 2015
የሶማሊያ ጎርፍ 2015

በማዕከላዊ ሶማልያ በለደወይን የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ አካባቢውን በማጥለቅለቁ፣ በተከሠተ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ 200 መቶ ሺሕ ሰዎች መፈናቀላቸውን ባለሥልጣናት ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡

ሂርና በተባለው ክልል በምትገኘው በለደወይን ያሉ ነዋሪዎች፣ በጣለው ከፍተኛ ዝናም ምክንያት ከተከሠተው ጎርፍ ለመሸሽ፣ ንብረታቸውን በራሳቸው ተሸክመው በጎርፍ ውስጥ ሲጓዙ ተስተውሏል።

“የሸበሌ ወንዝ መሙላት በአስከተለው ጎርፍ ምክንያት፣ እስከ አሁን 200 ሺሕ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ቁጥሩ በማንኛውም ሰዓት ሊጨምር ይችላል፤” ሲሉ፣ በሂርና ክልል የማኅበራዊ ጉዳይ ምክትል አስተዳዳሪ ዓሊ ሑሴን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ምክትል ገዢ ሓሳን አብዱሌ በበኩላቸው፣ በጎርፉ ሦስት ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጎርፉ አደጋ የተከሠተው፣ በተከታታይ ዓመታት ድርቅ ምክንያት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶማልያውያን ለረኀብ በተጋለጡበትና አገሪቱ ከእስላማዊ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋራ በመዋጋት ላይ ባለችበት ወቅት ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይም በአጋጠመው ጎርፍ፣ ነዋሪዎች በእኩለ ሌሊት ቤታቸውን ጥለው መውጣታቸውን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG