በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ 200ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ

በሶማሊያ ባልደወይን ከተማ በደረሰው የጎርፍ ውሃ ውስጥ ሴቶች ሲሄዱ ይታያሉ። የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰሱ የደረሰው ጎርፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) አስታውቋል።
በሶማሊያ ባልደወይን ከተማ በደረሰው የጎርፍ ውሃ ውስጥ ሴቶች ሲሄዱ ይታያሉ። የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰሱ የደረሰው ጎርፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) አስታውቋል።

በማዕከላዊ ሶማሊያ የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ አካባቢውን በማጥለቅለቁ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 200,000 ሰዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ ባለስልጣን አስታወቁ።

በሂራን ክልል፣ ቤልደወይን ከተማ የዘነበው ዝናብ፣ በከተማዋ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲወጡ እና በጎርፍ በተጥለቀለቁ ጎዳናዎች ላይ እቃቸውን በጭንቅላታቸው ተሸክመው መጠለያ ፍለጋ እንዲጓዙ አድርጓቸዋል።

"የሸበሌ ወንዝ ሞክቶ ቤልደወይን ከተማን በማጥለቅለቁ ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል" ያሉት የሂራን ክልል ምክትል አስተዳዳሪ ኦስማን ሁሴን፣ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል አመልክተው፣ ተፈናቃዮቹን ለመርዳት የተቻለው ሁሉ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም በጎርፉ አደጋ እስካሁን ሶስት ሰዎች መሞታቸውንም አመልክተዋል።

ይህ የጎርፍ አደጋ የደረሰው ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ድርቅ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሶማሌዎችን ለረሃብ ባጋለጠበት እና ሀገሪቱ ላለፉት አስርት አመታት ከእስላማዊ ታጣቂዎች ጋር ትግል እያደረገች ባለችበት ወቅት ነው።

XS
SM
MD
LG