በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ግጭት ለማቆም የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወራቶች ቢቆጠሩም፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚካሄዱ ግጭቶች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው። ለመሆኑ ለኢትዮጵያ መረጋጋት ስጋት ሆነው የቀጠሉ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ሀገሪቱን ወደ ሰላም እና እርቅ ሂደት ለመውሰድ የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ምን ያክል እንቅፋት ሆነዋል ስንል በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተንታኝ የሆኑትን ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የሚሲሲፒ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ዘነበ በየነን አነጋግረናቸዋል።
(ዝርዝሩን ከታች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)