በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ ሩሲያ የሚለው ቃል የሽብር አምሳያ ሆኗል አሉ


በዶኔስክ ዩክሬን በደረሰ የቦንብ ጥቃት ጉዳት የደረሰባት እና ቤቷን ያጣች እናት ከጎረቤቷ ጋር
በዶኔስክ ዩክሬን በደረሰ የቦንብ ጥቃት ጉዳት የደረሰባት እና ቤቷን ያጣች እናት ከጎረቤቷ ጋር

የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ በትላንትናው ዕለት ባደረጉት ዕለታዊ ንግግራቸው ሩሲያ የሚለው ቃል “የሽብር አምሳያ ቃል ሆኗል፤ ስለዚህም ላስከተለው ፍርሃት የሽንፈት እና የፍትሃዊ ቅጣት ምሳሌ ይሆናል” ብለዋል።

ዘለንስኪ አያይዘውም በትላንትናው ዕለት ሩሲያ ያደረሰችው የቦንብ ጥቃት “በኼርሶን ምግብ ለመግዛት የወጡ የሲቪሎችን ሕይወት ቀጥፏል፤ በጥቃቱ ሶስት ዩክሬናዊያን ሞተዋል” ብለዋል።

በተጨማሪም ዘለንስኪ “የቁማር እና የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም ከመንግስት ገንዘብ እያወጡ የሩሲያን ሴራ ሲደግፉ የነበሩ ዩክሬናዊያን” ናቸው ያሏቸውን 280 ኩባኒያዎች እና 120 ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ እሁድ ባወጣው የሩሲያ ዩክሬን የደህንነት መግለጫ ላይ ምንም እንኳን የደረሰው ጉዳት እንደ ሞስኮ እና ቅዱስ ፔተርስበርግ ባሉ ትላልቅ እና ባለጸጋ ከተሞች ላይ ባይታወቅም፤ ሩስያም ‘እጅግ ከባድ የሆነ ጉዳት’ ደርሶባታል ብሏል። በአንጻሩ በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍሎች ላይ የደረሰው የሞት አደጋ በሞስኮ ከደረሰው “30-40” እጥፍ ከፍተኛ ነው ሲል አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG