በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የሚሳይል ጥቃቷን ማባባሷ አይቀርም ተባለ


በሩሲያ የሚሳይል  ጥቃት የተጎዳ መንደር
በሩሲያ የሚሳይል  ጥቃት የተጎዳ መንደር

ሩሲያ ትናንት ሀሙስ የሚሳይል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ይበልጡን እየተደጋገመ መሄዱ እንደማይቀር አመልክቷል።

ትናንት ሩሲያ በተለያዩ የዩክሬን አካባቢዎች ላይ ብዛት ያለው ሚሳይል የተኮሰች ሲሆን ቢያንስ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል። በመቶ ሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል።የትናንቱ የሚሳይል ጥቃት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከደረሱት ሁሉ ብዛት ያለው መሆኑ ተዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሀሙስ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃል የሰጡ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የደህንነት ባለሥልጣናት የዩክሬኑ ጦርነት ወሳኝ ወቅት ላይ እየደረሰ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG