በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ የስርቆት ምርመራ ቡድን ፕሬዘዳንት ራማፎሳ ላይ ስህተት አላገኘሁም አለ


የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪካ የጸረ ሙስና ተቆጣጣሪ ቡድን ለሃገሪቱ ፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፤ ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ በገጠር መኖሪያ ቤታቸው በሚገኝ ሶፋ ውስጥ ካከማቹትና ከተዘረፈባቸው ገንዘብ ጋር ተያይዞ ምንም ዓይነት ለመሸፋፈን የሞከሩት ነገር የለም ብሏል።

የገንዘቡን ስርቆት ለመሸፋፈን ሞክረዋል በሚል በፕሬዘዳንት ራማፎሳ ላይ ጥርጣሬዎች ለወራት አጥልተው የቆዩ ሲሆን ሁኔታዎቹ ስራቸውን እስከመልቀቅ ሊያደርሷቸው የሚችሉ ነበሩ። የፕሬዘዳንቱ ቃል አቀባይ ቪንሴንት ማግዌንያ “ፕሬዘዳንቱ በምንም ዓይነት አሉታዊ ድርጊት ውስጥ አልተሳተፉም እንዲሁም በቢሯቸው የተቀበሉትን ቃልኪዳን አላፈረሱም” ሲሉ በድጋሚ መግለጫ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ ፖሊስ ራማፎሳ ገንዘቡን ከየት እንዳመጡትን እና ከተዘረፈባቸው በኋላ ምን እንዳደረጉ ምርመራውን ማድረጉን ስለሚቀጥል ራማፎሳ የዚህ ምርመራ ዋነኛ ትኩረት ሆነው ይቀጥላሉ።

እስካሁን ድረስ የምርመራው ይዘት ይፋ ባይደረግም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ግን የሪፖርቱን ቅጂ አግኝተዋል። በዚህ መሰረትም የፕሬዘዳንቱ የደህንነት ቢሮ ሃላፊ ጉዳዩ እንደተከሰተ ለፖሊስ ሳያሳውቁ በፊት በራሳቸው ምርመራ መጀመራቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG