በቱርክ እና በሶሪያ 7.8 በሬክተር የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከደረሰ ከአምስት ቀናት በኋላ የነፍስ አድን ሰራተኞች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ማውጣታቸውን ቀጥለዋል።
ይሁን እንጂ አንዳንድ የነፍስ አድን ስራዎች በአቅራቢያቸው በሚፈጸሙ ዝርፊያዎች የተነሳ ስራ መስተጓጎላቸው ተነገሯል።
እስካሁን ድረስም በቱርክ እና ሶሪያ ከ28,000 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ቤት አልባ መሆናቸውን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ሃላፊ ማርቲን ግሪፊዝ የሟቾች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
በአማፂያን ቁጥጥር ስር ያለው የሶሪያ ሰሜናዊ ምዕራብ ክልል በጉዳቱ እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳ አካባቢ ነው።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጂብ ጣይብ ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት ንግግር ኤርዶጋን የመሬት መንቀጥቀጡን “የክፍለ ዘመኑ አደጋ” ሲሉ ጠርተውታል።
የነፍስ አድን ቡድኖች በአደጋው ምክንያት የፈረሱ ህንጻዎች ፍርስራሽ ስር ሰዎችን የማዳን ሥራዎች ቀጥለዋል። ይሁን እንጂ
ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጡ ወቅት ለወደቁት ህንፃዎች ግንባታ ጥራት ተጠያቂ ናቸው የምትላቸውን በርካታ የግንባታ ተቋማትን ከትላንት ቅዳሜ አንስቶ ማሰር ጀምራለች።