በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱርክ ሁለት ድርጅቶች የነፍስ አድን ሥራቸውን ለጊዜው አቆሙ


ፎቶ ኤ.ኤፍ.ፒ (የካቲት 10, 2023)
ፎቶ ኤ.ኤፍ.ፒ (የካቲት 10, 2023)

በቱርክ የደረሰውን ርዕደ-መሬት ተከትሎ የነፍስ አድን ሥራ ሲያከናውኑ የነበሩ ሁለት የጀርመን ድርጅቶች ሥራቸውን ለጊዜው ማቆማቸውን ዛሬ አስታውቀዋል።

የጸጥታ ችግርና በቡድኖች መካከል የሚደረግ ግጭት ሥራቸውን ለጊዜው ለማቆም እንዳስገደዳቸው ድርጅቶቹ አስታውቀዋል።

ድርጅቶቹ እንዳሉት የቱርክ የሲቪሎች ጠባቂ ኤጀንሲ ሥራ ለመቀጠል የሚያስችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን ሲያረጋግጥ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ረቸብ ታይብ ኤልዶዋን ዛሬ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁን አስታውሰው፣ አንዳንድ የዘረፋ ሁኔታዎች መታየታቸውን አምነዋል።

የቱርክ ባለስልጣናት በቡድኖች መካከል ግጭት አለ ስለሚለው ወሬ አያነሱም።

በቱርክና በሶሪያ የደረሰው ርዕደ-መሬት እስከ አሁን ከ 23 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወት መቀጠፉ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG