የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በተቋሙ የአስተዳደር ፍርድቤት የግማሽ ግዜ ዳኛ ሆነ እንዲያገለግሉ የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ዳኛ ሰለሞን አረዳን ሾመዋቸዋል። ከሀያ አመታት በላይ የዳኝነት ልምድ ያላቸው ዳኛ ሰለሞን ሹመቱን ያገኙት ከ170 ሀገራት ከተወዳደሩ 380 አመልካቾች ተመርጠው ሲሆን ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት በዓለም አቀፍ ተቋሙ ሰራተኞች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን እና የመብት ጥሰቶችን ይዳኛሉ።