በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በወላይታ ዞን በ1 ሚሊዮን 450 ሺ ዶላር ወጪ የተገነባ ሆስፒታል አስመረቀች


የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ በወላይታ ሶዶ
የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ በወላይታ ሶዶ

ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ህዝቦች እና ብሄር ብሄረ ሰቦች ክልል ወላይታ ዞን የተገነባውን ሶዶ ክርስቲያናዊ አጠቃላይ ሆስፒታል መርቃ ከፍታለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በዐለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅቷ ( ዩ ኤስ ኤድ ) አማካይነት በሆስፒታሉ ለተሰራው አዲስ የቀዶ ጥገና ማእከል ማሰሪያ፡ አጅግ የተራቀቁ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች ለመግዛት እና ለሀኪም ቤቱ ሰራተኞች መኖሪያ ማሰሪያ የሚውል ከ77 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ለግሳለች፡፡ ሆስፒታሉ በየዐመቱ ከሃያ ሺህ ለሚበልጡ ኢትዮጲያውያን ህይወት አድን ህክምና እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

በአዲሱ የቀዶ ጥገና ማዕከል ምረቃ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የዩ ኤስ ኤድ ሚሽን ምክትል ዳይሬክተር ቲም ስታይን መስሪያ ቤታቸው በኢትዮጵያ የህጻናት እና እናቶች ሞትን ለመከላከል በየዐመቱ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG