በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ፖሊስ ገዳዮችን እያፈላለገ ነው


የናይጄሪያ ፖሊስ ገዳዮችን እያፈላለገ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:08 0:00

የናይጄሪያ ፖሊስ ገዳዮችን እያፈላለገ ነው

በኒጀር ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ የገበያ ስፍራ አራት ፖሊስና ሁለት ሰላማዊ ሰው ተኩሰው የገደሉትን ሰዎች ለመያዝ የሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ፖሊሶች አሰሳ ጀምረዋል።

ትላንት ማክሰኞ ሞተር ብስክሌት የያዙ ታጣቂዎች ከያር ቡሉቱ ከተባለች የገበያ ስፍራ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ የፖሊስ መኪና ላይ ተኩሰው ጥቃት ማድረሳቸውን የሶኮቶ ግዛት ፖሊስ አዛዥ ቃል አቀባይ ሳንሲ አቡበከር ገልፀዋል። በጥቃቱ ጥበቃ ላይ የነበሩ አራት ፖሊሶችና ሁለት ነጋዴዎች ተገድለዋል፡፡

“አንተን እያናገርኩ ባለሁበት በአሁኑ ሰዓት ወደዚያው እያመራን ነው፡፡ አደጋውን አስመልክቶ ቦታው ላይ ተገኝተን የተፈጸመውን ለመመልከት እየተንቀሳቀስን ነው፡፡” ሲሉ ፖሊስ ምርመራ ለማድረግ ወደ ስፍራው ማምራቱን ቃል አቀባዩ አቡብከር ዛሬ ረቡዕ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

አቡበከር ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) በሰጡት መግለጫ “ጥቃቱ፣ ምናልባት ባለፈው ሳምንት የፖሊስ ኃይሎች በአቅራቢያው በሚገኝ ወረዳ የሚገኙ ሽፍቶችን በመግደላቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተወሰደ የበቀል እርምጃ ሊሆን ይችላል” ብለዋል፡፡

ናይጄሪያ ሰዎችን አግተው ገንዘብ በሚጠይቁ የወሮበላ ቡድን ታጣቂዎች ተከታታይ የተኩስ ጥቃቶችን ሲፈፀምባት መቆየቷ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

ባለሥልጣናትም በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ የሚታየውን ይህን ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እየታገሉ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን በቅርቡ ጥቃቱ በአካባቢው እየተባባሰ መሆኑን ገልጾ የእርሻ ሥራዎችን በማስተጓጎል የምግብ ደህንነት ስጋት ቀውሶችን እያስከተለ መሆኑን ማስጠንቀቁ ተዘግቧል፡፡

/ቲሞቲ አቢዙ ከአቡጃ ያጠናቀረውን ዘገባ ሙሉ ክፍል ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG