የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ተዋጊዎች ተወካዮች በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በሽሬ እንደስላሴ ተገናኝተው በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል።
የሠላም ሥምምነቱ አደራዳሪዎች ወደ መቀሌ ተጉዘው ከክልሉ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ስለ ሠላም ሂደቱ ተወያይተዋል።
በሌላ በኩል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሠላም ሥምምነት ከተደረገ እና በአራት አቅጣጫዎች ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱት ሁሉም መንገዶች ከተከፈቱ ወዲ ከ2ሺህ 400 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆን ምግብ፣ የህክምና መሳሪያ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ሌሎች ህይወት አዳኝ አቅርቦቶችን ወደ ትግራይ ማድረሱን በድህረ ገፁ ላይ አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊነት አየር አገልግሎትም ለመጀመሪያ ግዜ መንገደኞችንና ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ ጭነቶችን ትግራይ ክልል ወደሚገኘው የሽሬ የአየር ማረፊያ የማጓጓዝ ሥራ እየሠራ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/