በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባሳንጆ መቀሌ ናቸው

ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ተዋጊዎች መካከል የሠላም ሥምምነት እንዲደረስ ለማስቻል በአፍሪካ ኅብረት የተሾሙት አደራዳሪ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክልል መቀሌ እንደገቡ የትግራይ ቴሌቭዥን በማኅበራዊ ገጹ አጋርቷል።

ኦባሳንጆ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እንደተቀበሏቸው የዜና አውታሩ አክሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሓት ተወካዮች አአአ ኅዳር 2/2022 በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሠላም ሥምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ ከአደራዳሪዎች መካከል አንዱ ወደ ትግራይ ሲያቀኑ የመጀመሪያው ነው።

XS
SM
MD
LG