በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ ዋና ከተማ የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ አደጋ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ


በሞቃዲሹ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጉዳት የደረሰባቸውን ለመርዳት በጥረት ላይ
በሞቃዲሹ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጉዳት የደረሰባቸውን ለመርዳት በጥረት ላይ

በሶማሊያ ዋና ከተማ በሞቃዲሹ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትላንት ቅዳሜ ማምሻውን አንድ አጥቶ ጠፊ ባደረሰው ጥቃት በርካታ ሰዎች የመቁሰል እና የሞት አደጋ ደረሰባቸው። የአሜሪካ ድምጽ በስልክ ያነጋገራቸው የሶማሊያ የጸጥታ ጉዳይ ባለስልጣናት፤ ጥቃቱ የተፈጸመው በጄነራል ዳጋባዳን ወታደራዊ ካምፕ አካባቢ እንደሆነና ከሟቾቹ መሃከልም ወታደራዊ ምልምሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

ለጥፋቱ አል ሻባብ ሃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቱ 100 ወታደሮችን ገድያለሁ ብሏል። ይሁን እንጂ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የሟቾቹ አሃዝ 15 እንደሆነ ነው የዘገቡት።

“በአዲሶቹ ምልምሎች እና በንጹሃን ዜጎች ላይ የተወሰነ ጉዳት ደርሷል” ሲሉ የሶማሊያ ወታደራዊ ባለስልጣን አዳን ያሬ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የገለጹ ሲሆን ምርመራው እንደቀጠለ መሆኑንም ጨምረው አስታውቀዋል።

በርካታ የሞቃዲሹ ነዋሪዎች ይህ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የሞርታር ጥቃት ነው ብለው የሚያምኗቸው ፍንዳታዎችን መስማታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቀዋል።

ይህ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት የተፈጸመው የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር እና የአካባቢው የጎሳ ታጣቂዎች በጥምረት በመሆን በመሃል ሸበሌ በአዳን ያባል ከተማ ዳርቻ ላይ 100 የሚደርሱ የአል ሻባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን ካስታወቁ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።

XS
SM
MD
LG