በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘በውጭ ሃገር የሚኖሩ ሕጻናት እነሱን የሚመስል ሰው በመጽሃፍት ላይ እንዲያገኙ ነው እቅዴ’ ማኅሌት ሰይፉ  

‘በውጭ ሃገር የሚኖሩ ሕጻናት እነሱን የሚመስል ሰው በመጽሃፍት ላይ እንዲያገኙ ነው እቅዴ’ ማኅሌት ሰይፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:41 0:00

‘በውጭ ሃገር የሚኖሩ ሕጻናት እነሱን የሚመስል ሰው በመጽሃፍት ላይ እንዲያገኙ ነው እቅዴ’ ማኅሌት ሰይፉ

የሃበሻ ልጅ ከወር በፊት ለህትመት የበቃ የሕጻናት መጽሃፍ ነው። ሃያ አራት ገጽ ያለው ይኸው መጽሃፍ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተጻፈ ነው። የመጽሃፉ ደራሲ ማኅሌት ሰይፉ ነዋሪነቷ በካናዳ ካደረገች አመታት አስቆጥራለች። ለሁለት አመት ሴት ልጇ መጽሃፍ በምታነብበት ጊዜ መጽሃፍቶቹ ላይ ኢትዮጵያዊ አለባበስ፣ አኗኗር አለመኖሩ እንዳሳሰባት እና ከዛ በመነሳት ልጇን እያሰበች መጻፏን ትናገራለች።

ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ ነገሮችን በትኩረት እንደሚያዩና እራሳቸውን የሚመስል አካባቢ ውስጥ አለመሆናቸውን ሲረዱ ይገለላሉ ትላለች። በተለይም በውጭ ሃገር የሚኖሩ ሕጻናት እራሳቸውን የሚመስል ሰው በመጽሃፍቱ ላይ የሚያዩበት አማራጭ ሊኖር ይገባል የምትለው ማኅሌት ልጄ ይሄ ስሜት እንዳይኖራት ተከታታይ መጽሃፍትን መጻፌ አይቀርም ብላለች።

/ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG