በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመቀሌ የአየር ድብደባ


የመቀሌ የአየር ድብደባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:09 0:00

የመቀሌ የአየር ድብደባ

የኢትዮጵያ መንግሥት “ሲቪሎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት ፈፅሟል” ሲል ህወሓት ከሰሰ።

የትግራይ የውጭ ጉዳዮች ቢሮ የተባለው አካል ባወጣው መግለጫ “መቀሌ ውስጥ ወታደራዊ ዒላማ በሌለበት የህፃናት መጫወቻ ሥፍራና መዋዕለ ህፃናት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል” ብሏል።

የመቀሌ ሪፖርተራችን የአይደር ሆስፒታል ኃላፊዎችን አነገግሮ በሰጡት መግለጫ ሁለት ህፃናትን ጨምሮ አራት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እንደነገሩት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ሲቪሎች ላይ የተፈፀመ ድብደባ አለመኖሩን ገልፆ ክሱን ማስተባበሉንና ዒላማው ወታደራዊ ተቋማት መሆናቸውን መናገሩን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

የአየር ጥቃቱ ዘገባ ከመሰማቱ በፊት የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ መንግሥት በትግራይ ክልል የሚገኙ የተመረጡ የሕወሃት ወታደራዊ ይዞታዎችን እንደሚመታ ገልፆ ሲቪሎች ወታደራዊ ትጥቆችና ማሰልጠኛዎች ከሚገኙባቸው አካባቢዎች እንዲርቁ መልዕክት አስተላልፎ እንደነበር ታውቋል።

ሁለቱም አካላት ግጭቱን በማቆም ለሰላም የሚደረጉ ጥረቶችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሃገር ውስጥ አካላትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ተማፅኖ እያሰሙ ቢሆንም ሁኔታው እስካሁን የመብረድ አዝማሚያ እንደሌለው ተዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መቀሌ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን “ህወሓት ዘርፎታል" የተባለውን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ እንዲመልስ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች ጥሪ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወርና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ አድራጎቱን አውግዘዋል።

ይሁን እንጂ ህወሓት ትናንት ባወጣው መግለጫ “ነዳጅ አልዘረፍኩም” ብሏል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG