በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትግራይ ጉዳይ ላይ የሰጡት አስተያየት “ሥነ ምግባር የጎደለው ነው” አለች


ኢትዮጵያ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትግራይ ጉዳይ ላይ የሰጡት አስተያየት “ሥነ ምግባር የጎደለው ነው” አለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:22 0:00

ኢትዮጵያ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትግራይ ጉዳይ ላይ የሰጡት አስተያየት “ሥነ ምግባር የጎደለው ነው” አለች

በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ “በዓለም አስከፊው ሰው ሰራሽ ሰብዓዊ ቀውስ ነው” ጉዳዩ ትኩረት ያላገኘው “በትግራይ ባሉ ሰዎች የቆዳ ቀለም ምክንያት ነው” ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ትናንት መናገራቸው “ሥነ ምግባር የጎደለው” እና “ቦታው ካለው ከፍተኛ ደረጃ አንጻር የማይመጥን ነው” ስትል ኢትዮጵያ ዛሬ መልስ ሰጥታለች።

የዓለም ጤና ድርጅቱ ኃላፊ እንዳሉት በትግራይ የሚኖሩ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኢትዮጵያና በኤርትራ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ግዜ ከበባ ውስጥ ቆይተዋል። ትግራይ ከውጪው ዓለም ተገልላ እንደ ኤሌክትሪክና ባንክ አገልግሎቶች በሌሉበትና፣ መጠነኛ ነዳጅ ብቻ በሚሰጥበት ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች ብለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ትናንት እንደተናገሩት ዓለም በቂ ትኩረት ያልሰጠው በትግራይ ባሉ ሰዎች “የቆዳ ቀለም” ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል።

“ካለ ምንም ማጋነን በትግራይ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ በዩክሬን ካለው ይበልጣል። ከብዙ ወራት በፊት ምናልባትም ምክንያቱ በትግራይ ያሉ ሰዎች የቆዳ ቀለም ሊሆን ይችላል ብዬ ነበር። ይህ በአሁኑ ወቅት በዓለም የሚታይ አስከፊ ቀውስ ነው። እኔ ከትግራይ ነኝ። ይህን የምለው ግን ከትግራይ ስለሆንኩ አይደለም። ይህ እውነታው ነው።” ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ “በዓለም አስከፊው ሰው ሰራሽ ሰብዓዊ ቀውስ ነው” ጉዳዩ ትኩረት ያላገኘውም “በትግራይ ባሉ ሰዎች የቆዳ ቀለም ምክንያት ነው ሊሆን ይችላል” ማለታቸው፤ “ሥነ ምግባር የጎደለው” እና “ቦታው ካለው ከፍተኛ ደረጃ አንጻር የማይመጥን ነው” ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ መልስ ሰጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG