በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከእረኝነት ወደ አለም ዓቀፍ የፊልም ባለሞያነት 


ከእረኝነት እስከ አለም ዓቀፍ የፊልም ባለሞያነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:36 0:00

ከእረኝነት እስከ አለም ዓቀፍ የፊልም ባለሞያነት

በሰሜን ተራሮች ስር ተወልዶ ያደገው ውበቱ ሺመላሽ የልጅነት ዘመኑን በእረኝነት፤ እንዲሁም አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ የውጭ ሃገር ዜጎች ጭነት ከብቶችን በማከራየት አሳልፏል። የራስ ዳሽንን ተራራ የተጓዦችን ቁሳቁሶች ተሸክሜ ከ20 ጊዜ በላይ ወጥቼዋለሁ ይላል።

ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መጥቶ የፊልም ጥበብ በማጥናት በሆሊውድ የራሱን መሰረት ጥሏል። ውበቱ የሰራቸው በግርዛት ዙሪያ የሚያተኩረው ‘ሰባሪ ምላጭ’ እና አለም አቀፍ የስደት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው ‘ካንትሪ ለስ ዉማን’ የተሰኙ ሁለት ፊልሞች በቅርቡ ከስምንት በላይ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ተቀዳጅተዋል።

ውበቱ ከዚህ በተጨማሪም የሰሜን ተራሮችን የሚያስጎበኝ ኤኮ ትሬክ የተሰኘ የአስጎብኚ ተቋም አጋር- መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚም ነው። ይህ ተቋም ለትርፍ የተቋቋመ ይሁን እንጂ የአካባቢውን ማኅበረሰብ እያገዘ ይገኛል። ለአብነት በተቋሙ አማካኝነት 9000 የሚደርሱ የሶላር መብራቶች ለአካባቢው አርሶ አደር ቤተሰቦች ተከፋፍለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በድጋሚ ታጥበው በጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎችንም ለአካባቢው ልጃገረዶች ያከፋፍላል። ለዚህ ደግሞ ምክንያት የሆነው የልጅነት ተሞክሮው እንደሆነ ውበቱ ይናገራል። እሱ ተማሪ በነበረበት ዘመን ላይ ልጃገረዶች ልብሳቸውን የወር አበባ ሲነካቸው ይሳቅባቸውና እንዲሸማቀቁ ይደረግ እንደነበር ያስታውሳል። "ያኔ በልጅነቴ ባለማወቅ እኔም እራሴ አብሬ እስቅ ነበር አሁን ሳስበው ግን ይጸጽተኛል" ይላል። ስለዚህም የአካባቢው ልጃገረዶች ቅያሪ የውስጥ ልብስ እና የንጽህና መጠበቂያ እንዲኖራቸው ይሰራል። የመንደሩ እናቶች የእጅ ስራ ውጤቶችም ገበያ እንዲያገኙ በተቋማቸው ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። በእነዚህ አገልግሎቶቹ የተነሳም ወደዛ አካባቢ ጎራ ብትሉ ስም ከተጠራ መስተንግዶው ይደራል ይሄም ተቋማችን ትልቅ ስም እንዲኖረው አድርጎታል ይላል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG