በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የአፍሪካ መሪዎችን ዋሺንግተን ላይ ይሰበስባሉ


US President Joe Biden
US President Joe Biden

ከፊታችን ታኅሣስ 4 እስከ ታኅሣስ 6 / 2015 ዓ.ም. ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚጠራው “የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ” ላይ የአፍሪካ መሪዎችን ሁሉ እንደሚያስተናግዱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ አስታውቀዋል።

ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ዛሬ ያወጣው የፕሬዚዳንቱ መግለጫ “ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ያላትን ቁርጠኛነት የሚያሳይ፣ የአሜሪካና የአፍሪካን ግንኙነት ፋይዳ የሚያጎላ፣ የቅድሚያ ትኩረት በሚሰጣቸው ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ላይ ትብብርን የሚያጠናክር ይሆናል” ብሏል።

“የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ በጋራ እሴቶቻችን ላይ ተመሥርቶ አዲስ የምጣኔኃብት ግንኙነቶችን ያጎለብታል” ያሉት ባይደን አሜሪካና አፍሪካ “ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያድስ” ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

ጉባዔው “የኮቪድ-19ና ወደፊት የሚከሰቱ ወረረሽኞችን ጫናዎች ለመቀነስና ዓለምአቀፍና የአካባቢውንም ጤና ለማጠናከር በትብብር ለመሥራት እንደሚያግዝ” ፕሬዚዳንቱ አመልክተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ጉባዔው “የምግብ ዋስትናን፣ ሰላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ቀውስ ምላሽ ለመስጠት፣ ከዳያስፖራ ማኅበረሰቦች ጋር ያለውን ትስስር ለማጎልበት ይኖሩታል”ያሏቸውን ጥቅሞች ዘርዝረዋል።

“ከአፍሪካ መንግሥታት፣ ከሲቪል ማኅበረሰቡና በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ካሉት የዳያስፖራ ማኅበረሰቦች አባላት ጋር አብሮ ለመሥራት በጉጉት እጠባበቃለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንት ባይደን የግሉ ዘርፍም የጋራ እሴትና ራዕዮችን በማጎልበት የወደፊቱን የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪካ ግንኙነት ማጠናከሩን እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG