በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የዓለምን የምግብ ቀውስ ለማስወገድ በቂ ጥረት እያደረገች አይደለም ስትል አሜሪካ ወቀሰች


የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) አስተዳዳሪ ሰማንታ ፓወር
የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) አስተዳዳሪ ሰማንታ ፓወር

የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) አስተዳዳሪ ሰማንታ ፓወር ምሥራቅ አፍሪካ ላይ የተከተሰተውን የምግብ ቀውስ ለማስወገድ አገሮች ይበልጥ እንዲተጉ በማሳሰብ በቂ ጥረት እያደረገች አይደለችም ያሏት ቻይንና ነጥለው ወቅሰዋል፡፡

የሩሲያው የዩክሬን ወረራ የምሥራቅ አፍሪካ የምግብ ቀውስ እንዲባባስ አድርጓል ሲሉ ፓወር ከስሰዋል።

በዋሺንግተን የስትራቴጂክና ዓለምአቀፍ ጥናት ማዕከል መድረክ ላይ አስተዳዳሪዋ ትናንት ባሰሙት ንግግር በምሥራቅ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው የሰብዓዊነት ጥረት ላይ ቻይና “ተሣታፊ ባለመሆን ተለይታ ትታያለችች” ማለታቸው ተመልክቷል፡፡

ቻይና ተጨማሪ ምግብና ማዳበሪያ ወደ ዓለምአቀፍ ገበያው ወይም ወደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ብትልክ ኖሮ “በምግብና ማዳበሪያ ዋጋ ላይ ያለውን ጫና በማቃለል ዓለምን ለመምራት ያላትን ፍላጎትና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ያላትን ወዳጅነት ባሳየች ነበር” ብለዋል ሳማንታ ፓወር።

ለፓወር ንግግር ቻይና ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠችም፡፡

ሩሲያ ዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ያላወገዙ አገሮችንም በመተቸት ውጤቱ በዓለም የምግብ ገበያ ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉን ፓወር ጠቅሰዋል፡፡

የዩኤስአይዲ አስተዳዳሪ አክለው “ከዚህ ጦርነት ተገልለው የተቀመጡ አገሮች በዓለም ገበያ ካለው የምግብ ቀውስ ውጭ ተገልለው አልተቀመጡም” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG