በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጠበቃው በኩል የክስ መቃወሚያ አቀረበ


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጠበቃው በኩል የክስ መቃወሚያ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጠበቃው በኩል የክስ መቃወሚያ አቀረበ

ዛሬ ጠዋት የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረበው የፍትሕ መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ፣ “ከአንድ ዓመት በፊት በፍትሕ መጽሔት በወጡ ጹሑፎች ክስ ሊመሰረትብኝ አይገባም” የሚል መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን ችሎቱ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 26 ቀጥሯል፡፡

በሌላ ዜና፣ ፖሊስ “ሰው እየሞተ እንዴት ችግኝ ይተከላል” የሚል የቅስቀሳ ይዘት ያለው መልዕክት በማኅበራዊ ገጹ አስተላልፏል በሚል ጠርጥሬዋለሁ ብሎ የያዘው የ“አል ዐይን ኒውስ” ጋዜጠኛ አልአዛር ተረፈ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

ባለፈው ሐሙስ ሐምሌ ሰባት የተያዘው አልዓዛር፣ በማግስቱ ዓርብ ዕለት በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ታይቶ በ5 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ተወስኖለት ነበር፡፡

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG