በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እና ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል 40 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ



የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እና ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል 40 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:33 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እና ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል 40 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ለዩክሬን የሰብዓዊ እና ወታደራዊ ርዳታ እንዲውል የተጠየቀውን የ40 ቢሊየን ዶላር ረቂቅ ህግ አፅድቋል። በአንድ ሳምንት የዘገየው ይህ የምክር ቤቱ ውሳኔ፣ በአመቱ መጀመሪያ ፀድቆ የነበረው በቢሊየኖች የሚቆጠር ርዳታ እያለቀ ባለበት ወቅት፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ረቂቅ ህጉን በፊርማቸው ቋሚ ህግ ለማድረግ ያስችላቸዋል።

ለዩክሬን የሚሰጠው ርዳታ የደረሰው በትክክለኛው ግዜ ነው። ምክንያቱም የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መጋቢት ወር ላይ አሳልፎት የነበረው የ14 ቢሊየን ወታደራዊ እና ሰብዓዊ ርዳታ ወደ ማለቁ ተቃርቦ ነበር። አዲሱ ግዙፍ የእርዳታ ጥቅል ያለፈው ታዲያ ፓርቲዎች የጋራ ድጋፍ ባሳዩበት 86 ለ11 በሆነ ድምፅ ነው።

ህጉን ተቃውመው ድምፅ የሰጡት 11 ሴናተሮች ሪፐብሊካኖች ሲሆኑ ሴናተር ራንድ ፓውል የአሜሪካ መንግስት ርዳታውን በምን እንደሚቆጣጠረው ማብራሪያ እንዲሰጥ በመጠየቃቸው ረቂቅ ህጉ መፅደቅ ከነበረበት ግዜ በአንድ ሳምንት እንዲዘገይ አድርገዋል። ሌሎች ደግሞ በአሜሪካ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በታየበት ወቅት ይህን ያክል ገንዘብ ወደ ዩክሬን መላክ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የዲሞክራት ፓርቲ አብላጫ መሪ ሴናተር ቻክ ሹመር "እኛ አሜሪካኖች፣ ዲሞክራቶት እና ሪፐብሊካን፣ ሁላችንም - ቭላድሚር ፑትን በዩክሬናውያን ህዝቦች ላይ አረመናዊ ጠብ ጫሪነቱን እየቀጠለ፣ ሲቪሎች በሚታከሙበት ሆስፒታሎች ላይ እየተኮሰ፣ ህፃናትን እና ንፁሃንን ኢላማ አርጎ እየጎደለ ችግር እንደሌለ አንገታችንን አቀርቅረን ልንቀመጥ አንችልም። ይህ ያክል ቁጥር ያላቸው ሪፐብሊካኖች ጥቅሉን ሲቃወሙ ግን በውጪ ላሉ ጠላቶቻችን የምናስተላልፈው መልዕክት ግን ይህንን ነው" ብለዋል።

ከፀደቀው የእርዳታ ገንዘብ 900 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው ዩክሬናዊ ስደተኞችን ለመርዳት የሚውል ሲሆን 4.4 ቢሊየን የሚሆነው ደግሞ በሀገሪቱ የታየውን የምግብ አቅርቦች ችግር ለመፍታት የሚውል ይሆናል።

ዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ወደ ዩክሬን ለማስተላለፍ የሚረዳ ተጨማሪ 100 ሚሊየን ዶላርም አፅድቃለች። የርዳታ ገንዘቡ የባይደንን ፊርማ እንዳገኘ ወዲያውኑ ወጪ የሚደረግ ሲሆን ሩሲያ በየካቲት ወር ወረራ ከፈፀመች ጊዜ አንስቶ ዩናይትድ ስቴትስ 54 ቢሊየን ዶላር ርዳታ ለዩክሬን ልካለች።

XS
SM
MD
LG