አለማችን ከምንግዜውም በላይ እየሞቀች ነው። ይህ የሙቀት መጠን መጨመር ደግሞ በርካታ ስጋቶችን ፈጥሯል። በተለይእንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀራት ውስጥ የሚታየው የዝናብ ወቅት መዛባት፣ ያልተለመደ ከፍተኛ ዝናብ እና ጎርፍ ወይምከመጠን ያልፈ ሙቀት፣ በግብርና እና በከብት ርባታ የሚተዳደረውን ህብረተሰብ ለድርቅና ረሃብ አደጋ አጋልጧል።
ይህ በከባቢ የአየር ሙቀት መጨመር ምክንያት እየደረሰ ያለውን የአየር ንብረት ለመዋጋት እንደመፍትሄ ከተቀመጡመፍትሄዎች አንዱ ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ በጉዳዩ ላይ እውቀት እንዲኖራቸው በማድረግ፣ የአየር ንብረትለውጡን ያገናዘበ አኗኗር እንዲያዳብሩ ማድረግ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ይመክራሉ።
ለመሆኑ በኢትዮጵያ የሚገኙ ተማሪዎች ስለ አየር ንብረት ለውጥ ምን ያክል ያውቃሉ?
በኮከበ ፅብሃ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ስንዱ አበበ፣ የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ስለአካባቢጥበቃም ሆነ ስለ አየር ንብረት ለውጥ ያላት እውቀት እምብዛም ሲሆን የምታስታውሰው በጆግራፊ ትምህርት ውስጥስትማር የሰማቻቸውን ነው።
ስንዱ እንደምትለው በኮከበ ፅብሃ የፆታ፣ የሚኒ ሚዲያ እና የመሳሰሉ ክለቦች ቢኖሩም፣ በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የሚሰራክለብ ግን ሰምታ እንደማታውቅ ትናገራለች።
ሌላው ያናገርነው ተማሪ ሚካኤል ተሾመ ይባላል። በአዲስ አበባ በሚገኘው አንድነት ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ስለአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ፅንሰ ሀሳብ ምን ያክል ያውቅ እንደሆነጠይቄው ነበር።
ሚካኤል በተወሰነ መጠንም ቢሆን ስለአየር ንብረት ለውጥ እውቀት ሊያገኝ የቻለው ከጆግራፊ ትምህርት እና በትምህርትቤቱ ውስጥ ተማሪዎች ባቋቋሙት የአካባቢ ጥበቃ ክበብ አባል በመሆኑ መሆኑን ገልፆልኛል።
በቦሌ ኮምዩኒቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩት መምህር ሙሉጌታ ታያቸው በበኩላቸው በትምህርት ቤታቸውውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያደርግ የአካባቢ ጥበቃ ክለብ መኖሩን ገልፀው በክለቡ ከሚንቀሳቀሱ ተማሪዎች ውጪ ግንተማሪዎች ስለአየር ንብረት የሚማሩበት አጋጣሚ ውስን መሆኑን ያስረዳሉ።
በአንድ ወቅት በደን ተሸፍነው የነበሩት የኢትዮጵያ ተራራማ ቦታዎች በህዝብ ብዛት ቁጥር መጨመርና ያንን ተከትሎበሚመጡ የእርሻ መስፋፋቶች አሁን ተራቁተዋል። ዝናብ በተለመደው መልኩ ወቅቱን ጠብቆ አይጥልም። ህልውናዋከተፈጥሮ ሀብት ለተያያዘው ኢትዮጵያ ደግሞ ይህ ትልቅ ስጋት ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ሚኖሶታ ዩንቨርስቲ የትምህርት፣ ፆታና፣ አየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ የሆኑት ክርስቲና ክዎክየአየር ንብረት ለውጥና ተያይዥ ጉዳዮችን በትምህርት ቤት በመደበኛነት ማስተማር፣ ተማሪዎች ማህበረሰባቸውንእንዲረዱ እና ለውጡን ያማከለ አኗኗር ይዘው እንዲያድጉ ይረዳቸዋል ይላሉ - በተለይ ደግሞ ሴት ተማሪዎች
"ሴት ተማሪዎች በተለይ እራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን አደጋ ላይ በትምህርት ቤት ወደ አመራር ቦታ እንዲመጡበማበረታታት እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ እራሳቸው እናማህበረሰባቸው ላይ አደጋ የተደቀነውን አደጋ በተወሰነ መልኩ እንዲቀንሱ ማድረግ ይቻላል። ለውጡ ያመጣውን የአካባቢናየኢኮኖሚ ሁኔታ ቀድመው ተረድተው እራሳቸውን ቀድመው ዝግጁ ያደርጋሉ። "
ባለሙያዋ እንደሚሉት፣ ስለአየር ንብረት ለውጥ ተማሪዎችን በክፍል ውስጥ ማስተማር ብቻ በቂ አይሆንም። ተማሪዎችተቋማት ችግሩን ለመፍታት ስለሚያደርጓቸው ጥረቶች እንዲያውቁና የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ማብቃትም የትምህርትቤቶች እና የመምህራን ሀላፊነት ሊሆን ይገባል ይላሉ።