በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ዳግም ተጀመረ


በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ዳግም ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:46 0:00

ዛሬ በሦስት በረራዎች ከ1 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመልሰዋል

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ቤት እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በዘመቻ የማስመለስ ተግባር ሲካሔድ የአሁኑ ለ4ኛ ዙር እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋራ በተደረሰ ስምምነት መሰረት የተጀመረው የአሁኑ ዜጎችን የማስመለስ ተግባር፣ በሳምንት ውስጥ በሦስት ቀናት ዘጠኝ በረራዎችን በማድረግ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል፡፡

ዛሬ የተመለሱ ዜጎች በአየር መንገድ አቀባበል ከተደረግላቸው በኋላ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ሞክረን የነበረ ሲኾን፣ ከአስተባባሪዎቹ ሁኔታዎች ሊመቻቹልን ባለመቻሉ ፣ አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡

ይኹን እንጂ፣ “ለሦስ ዓመት እና ከዚያም በላይ በሳዑዲ አረቢያ መታሰራቸውን እና ለተለያየ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋልጠው መቆየታቸውን” አንዳንድ ተመላሾች ከአውሮፕላን በሚወርዱበት ወቅት ነግረውናል፡፡

አሁንም በርካታ መሰል ችግር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡

የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና ሀገራት፣ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ እስከሞት የሚደርስ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ በተለያዩ ጊዜያት መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

ከእዚህ መካከል የሆነው ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ የሳዑዲ ድምበር ጠባቂዎች ከመጋቢት 2014 እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ “የየመን እና የሳዑዲ ድንበርን ለማቋረጥ የሞከሩ በትንሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ገድለዋል” ማለቱ አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG