በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመብቶች ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ ምርመራ ኮሚሽነሮችን ሰየመ


የመብቶች ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ ምርመራ ኮሚሽነሮችን ሰየመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00

በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ተግባራትን እንዲመረምር ለተቋቋመው ኮሚሽን አባላት ተሰየመ

በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ቤት ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ተግባራትን እንዲመረምር ለተቋቋመው ኮሚሽን አባላትን ሰየሙ።

የምክር ቤት ፕሬዝዳንት አምባሳደር ፌዴሪኮ ቪሌጋስ፣ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር ለተቋቋመው፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ ፣ 3 ግለሰቦችን በአባልነት ሰይመዋል፡፡

የኮሚሽኑ አባላት ሆነው እንዲያገለግሉ የተሾሙት ጋምቢያዊቷ ፋቱ ቤንሱዳ፣ ኬንያዊቷ ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ እና አሜሪካዊው ስቲቨን ራትነር ሲሆኑ፣እንደ አውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2012 እስከ 2021 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ሆነው ያገለገሉት ቤንሱዳ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሆነው ያገለግላሉ ተብሏል።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በወቅቱ ባወጧቸው መግለጫዎች በሰብዓዊ ምክር ቤቱ የሚቋቋመው ኮሚሽን የሚያደርገው አዲስ ምርመራ እንደሌለ በመግለጽ ውሳኔውን መቃወማቸው ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለውሳኔው ስኬታማነት ትብብር እንደማያደርግም አስታውቋል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG