አዲስ አበባ —
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተከትሎ የመንግሥቱን መደበኛ ሥራዎች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲመሩ ተወስኗል።
“የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት በህዝቡ ዘንድ መነቃቃት ፈጥሯል” ብሏል የመንግሥት ከምዩኒኬሽንስ አገልግሎት።
መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እንደሚያደናቅፍ ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች አካላት ሥጋታቸውን እየገለፁ መሆናቸው ይታወቃል።
በሌላ በኩል “ዣን አፍሪክ” የተባለ በፈረንሳይኛ የሚወጣ መፅሔት “ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ያላሉትን እንዳሉ በማስመሰል አውጥቷል” ያሉትን ሪፖርትም የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ተችተዋል።
በሌላ በኩል ዠን አፍሪክ የተባለ የፈረንሳይኛ መጽሔት በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን በስልክና በኢሜል ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምላሻቸውን አላገኘንም።
/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/