No media source currently available
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተከትሎ የመንግሥቱን መደበኛ ሥራዎች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲመሩ ተወስኗል። “የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት በህዝቡ ዘንድ መነቃቃት ፈጥሯል” ብሏል የመንግሥት ከምዩኒኬሽንስ አገልግሎት። መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እንደሚያደናቅፍ ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች አካላት ሥጋታቸውን እየገለፁ መሆናቸው ይታወቃል።