በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀገራዊ እሴቶችን ለመገንባት ግብረ-ገብ ትምህርት ወሳኝ ነው - ምሁራን


ሀገራዊ እሴቶችን ለመገንባት ግብረ-ገብ ትምህርት ወሳኝ ነው - ምሁራን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ፣ የግብረ ገብ ትምህርት እንደ አዲስ እንደሚጀመር ማስታወቁ መጪው ትውልድ እንደ ሀገር ለመቆም የሚያስችለው የጋራ እሴቶችን ለመገንባት እንደሚረዳ ምሁራን ተናግረዋል። ትምህርቱ መሰጠት ሲጀምርም ሁሉንም ማህበረሰብ ባማከሉ ሰብዓዊ እሴቶች ላይ ትኩረት እንዲደረግም መክረዋል። ለመሆኑ የግብረ ገብ ትምህርት ምን ማለት ነው? በአዲሱ የትምህርት ስርዓት ውስጥ መካተቱስ ለሀገር ግንባታ ምን ሚና አለው?


ከሁለት አስርት አመታት በላይ ኢትዮጵያ ስትከተለው የነበረውን የትምህርት ስርዓት በአዲስ የተካው ፍኖተ ካርታ ቅደመ አንደኛ ደረጃ፣ አንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ በሚል እርከን በከፋፈላቸው ሁሉም የትምህርት መስኮች የግብረ ገብ ትምህርት ለመጀመር ተዘጋጅቷል።

ለመሆኑ ይህ የግብረ ገብ ትምህርት ምን ማለት ነው? ምን አይነት አስተምሮዎችንስ ያካትታል? በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል የሚያስተምሩት ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ያብራራሉ።

የግብረ ገብ ትምህርት ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። ለመጀመሪያ ጊዜ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲሰጥየተደረገው በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ሲሆን፣ በስነምግባር የታነፀ ትውልድ የመፍጠር አላማ ነበረው። ሆኖም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል የሚያስተምሩት ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ በወቅቱ የነበረው ትምህርት ጥቅም ቢኖረውም ሁሉን አካታች ግን አልነበረም ይላሉ።

ቀጥሎ የመጣው የደርግ ስርዓት የግብረ ገብ ትምህርትን ከሀይማኖት መነጠል ቢችልም፣ በምትኩ መንግስት በወቅቱ ይከተለው የነበረው ርዕዮተ ዓለም ማስተማሪያ በማድረጉ የግብረገብ ትምህርት ዓላማ መስመሩን ሳተ ይላሉ - ፕሮፌሰር በቀለ። ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላም የሥነ-ዜጋ ትምህርት ተብሎ ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ይህም የፖለቲካ አመለካከትን ለማስረፅ የዋለ እንጂ ስነ-ምግባርን ያስተማረ እንዳለሆነም ይከራከራሉ።

ለመሆነ የግብረ ገብ ትምህርት ለተማሪዎች መሰጠት የሚያስፈልግበት አላማው ምንድነው? አዲሱን የትምህርት ፍኖተካርታ ይዘት በቅርበት የተከታተሉትና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሥነ-ልሳን ትምህርት ክፍል መምህርና ጥናት አጥኚየሆኑት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ምላሽ አላቸው።

ዶክተር በድሉ አክለው በነዚህ ሰብዓዊ የሆኑ መሰረቶች ላይ የተመረኮዘ የግብረ ገብ ትምህርት- ከፖለቲካ አስተሳሰብ የፀዱና በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ እሴቶችን ለማስተማር እንዲሁም ከስር መሰረቱ በመልካም ስነ-ምግባር የተገነባ ትውልድን ለመፍጠር ያስችላል ሲሉ በምሳሌ ያስረዳሉ።

ይህ ወጣቶችን በሥነ-ምግባር የማነፁ ተግባር በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ መካተቱ አንድ እርምጃ መሆኑን የሚስማሙትምሁራን የትውልድ የሥነ-ምግባር ክፍተት የሚሞላው ግን በትምህርት ቤት በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በሚሰጥትምህርት እንዳልሆነ ያሰምሩበታል። ፕሮፌሰር በቀለ እንደሚሉት ከመምህራን ጀምሮ ስልጣን ላይ እስካሉ አመራሮችድረስ ተግባራዊ ሀላፊነት አለባቸው።

ዶክተር በድሉም በዚህ ይስማማሉ። በወላጅና አካባቢ፣ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት የተደገፈ የግብረ ገብ ትምህርት- በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ በብዙ ውጥረት ውስጥ ባለ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ወጣቶች ተስማምተውና ተከባብረውእንደሀገር ለመቆም የሚያስችላቸውን የጋራ ማህበራዊ እሴቶችን ለመፍጠር ቁልፍ መሰረት መሆኑን ያሰምሩበታል።

በያዝነው የ2014 ትምህርት ዘመን ተግባራዊ እንዲደረግ የሚጠበቀው አዲሱ የትምህርት ስርዓት ከግብረ ገብነትበተጨማሪ አገር በቀል እውቀት፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባ፣ ጥናትና ምርምርንም እንደሚያበረታታ ፍኖተ ካርታው ያትታል። ለሚቀጥሉት አምስት አመታትም ተግባር ላይ ይውላል።
XS
SM
MD
LG