በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ገላ የሚያጥቡት በጎ ፈቃደኞች


የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ገላ የሚያጥቡት በጎ ፈቃደኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00

"የጎዳና ላይ ሻወር" ተብሎ የሚታውቀው የበጎ ፈቃደኞች ቡድን፣ በዐዲስ አበባ ከተማ "አሜሪካን ግቢ" እየተባለ በሚጠራው ሰፈር፥ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ገላ እያጠበ ንጹሕ ልብስ በማልበስ፣ በማሳከም እና በመመገብ፣ እንዲሁም ለማደሪያቸው አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የቆርቆሮ ቤት ሠርቶ በመለገስ ይታወቃል። በተጨማሪም ቡድኑ፣ ለሰፈሩ ችግረኛ ቤተሰቦች፥ የምገባ፣ የአልባሳት እና የሕፃናት የትምህርት ቤት ክፍያ ድጋፎችን ያደርጋል።

ዕለት ዕለት ያለማቋረጥ የምገባ መርሐ ግብር የሚያካሒደው የበጎ ፈቃደኞች ቡድኑ፣ ገባሬ ሠናይ ግለሰቦች በሚያደርጉለት ድጋፍ እንዲሁም እንደ ሠርግ እና ኀዘን ያሉ ማኅበራዊ ኹነቶቻቸውን አብረው ለማሳለፍ የሚሹ ግለሰቦች በሚያደርጉለትም እገዛ በጎ ሥራዎቹን ይከውናል።

ኤደን ገረመው የበጎ ፈቃድ ቡድኑን መሥራቾች እና የመርሐ ግብሩን ተጠቃሚ አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ ይቀጥላል።

XS
SM
MD
LG