በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ኢትዮጵያ 11ኛ ክልል የምትመሰርትበት ድምጽ በ”ሕዝበ ውሳኔ” መገኘቱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ኢትዮጵያ 11ኛ ክልል የምትመሰርትበት ድምጽ በ”ሕዝበ ውሳኔ” መገኘቱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ

የኢትጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፣ መስከረም 20 በተካሔደው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ በደቡብክልል የሚገኙ 5 ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ በአዲስ ክልል ለመደራጀት የሚያስችላቸውን ከፍተኛ ድምጽ አግኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ አዲስ ክልልለማደራጀት ሕዝበ ውሳኔ ሲካሔድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕዝበ-ውሳኔ በታሪክ ሁለተኛው ነው፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ከነበሩበት የደቡብ ክልል በመነጠል የጋራ አንድ ክልል ለመመስረትአሊያም በክልሉ ለመቆየት፣ መስከረም 20/2014 ዓ.ም ያካሔዱት ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት ሕዝበ ውሳኔው የተካሔደባቸው አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ፡ማለትም የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ፣ የዳውሮ እና የሸካ ዞኖች እና የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት የሚያስችላቸውንከፍተኛ ድምጽ አግኝተዋል፡፡

በሕዝበ ውሳኔው በአጠቃላይ ከተሰጠው 1262659 ድምጽ ውስጥ ከጥቂት የተበላሹ እና ሌላ እንከንየተገኘባቸው የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ውጭ ከ1ሚሊዮን 221 ሺህ በላይ ድምጽ ሰጪዎች አዲስ ክልል እንዲመሰረት መምረጣቸውንየቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ገልጸዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ኢትዮጵያ 11ኛ ክልል የምትመሰርትበት ድምጽ በ”ሕዝበ ውሳኔ” መገኘቱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:07 0:00


XS
SM
MD
LG