በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደንን ትዕዛዝ ኤርትራ አወገዘች፤ ህወሓት እንደሚደግፈው አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግጭት “እንዲራዘም ሰበብ በሚሆኑ ተጠያቂዎችና ተባባሪዎቻቸው ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል” በሚል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ዓርብ ያወጡትን ትዕዛዝ የኤርትራ መንግሥት ኮንኗል።

በሌላ በኩል ህወሓት ትናንት ባወጣው መግለጫ ትዕዛዙን እንደሚደግፍ ገልፆ እንዲያውም “እጅግ የዘገየ ቢሆንም ለአካባቢው ቀውስ መፍትኄ የሚያስገኝ ይሆናል” ብሎታል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዕለቱ ባወጡትና ለፕሬዚዳንት ባይደን ይድረስ ባሉት “ግልፅ ደብዳቤ” የዩናይትድ ስቴትስ ተከታታይ አስተዳደሮች በኢትዮጵያ ላይ “ይዘዋቸዋል” ባሉት “የተዛባ አመለካከት” ቅሬታ አዘል መልዕክት አስተላልፈው “ኢትዮጵያ ከሚሊዮኖች ደኅንነት ይልቅ ሥልጣንን መጠቅለልን በሚመርጡ የተከፉ ሰዎች የተቀነባበረ ተፅዕኖ ለሚያስከትላቸው መዘዞች አትንበረከክም” ማለታቸው ተዘግቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የባይደንን ትዕዛዝ ኤርትራ አወገዘች፤ ህወሓት እንደሚደግፈው አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:51 0:00


XS
SM
MD
LG