በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጥቂት ቀናት ውስጥ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ስለተሰበሰበበት ልዩ ዘመቻ


ኡስታዝ ጀማል በሺር
ኡስታዝ ጀማል በሺር

በአባይ ወንዝ ላይ በመሰራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ፣ የቅርብ ዓመታት የእሰጥ አገባ፣ የድጋፍ እና የተቃውሞ አውድማ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት የማህበራዊ መገናኛ ገጾች እና የአንተርኔት አውታሮች ናቸው። ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ግድቡን በተመለከተ በአረቡ ሀገር ያሉ ዕይታዎችን ለመፈተሽ የከፈቱት አውታር ከእነዚህ መካከል ይጠቀሳል።ስሙም የአባይ ንጉሶች ይባላል። ኡስታዝ ጀማል በዚህ የምስል ገጽ ላይ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲያነቁ ይውላሉ። ከሰሞኑ ደግሞ ትኩረትን ያገኘ ዘመቻን መርተዋል።

በመገንባት ላይ ባለችው ግድብ ሰበብ ዓለም አቀፍ ውዝግብ ውስጥ የገባችው ኢትዮጵያ ፣ ግድቡን ለመጨረስ የሚያስፈልገውን ከ 4 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ በዋነኝነት ለማግኘት የወጠነቸው በህዝብ መዋጮ ነው። በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ -ኢትዮጵያዊያንም የብዙሃን ትኩረትን ያገኘውን የድጋፍ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ለመጀመር የተነሱት - አስር ዓመታትን የዘለቀው ትብብር አካል ለመሆን ነበር።

የገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብሩ የመጀመሪያ ዕቅድ 50ሺ የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰብ ነበር ። ይሁንና እና የእንቅስቃሴው መጀመር የአረቡ ዓለም በሚያዘወትራቸው የዜና አውታሮች ዘንድ ትኩረትን ማግኘቱ ተጨማሪ ሰዎች እንዲረባረቡ ግፊት መፍጠሩን ኡስታዝ ጀማል ያስታውሳሉ።ይሄ መነቃቃት የኃላ ኃላ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 500ሺ የአሜሪካ ዶላር (ከ20 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ) እንዲሰበሰብ አስችሏል። ይሄ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የተሰባሰበው ገንዘብ ብዛት ከ700ሺ ዶላር (30 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ) ማለፉ ተሰምቷል። ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ !

ከ30 ሚሊየን በላይ ብር ስላሰባሰበው የትውልደ- ኢትዮጵያኑ ልዩ ዘመቻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00


XS
SM
MD
LG