በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዲስ ስታንዳርድ ላይ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ አነሳ


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዲስ ስታንዳርድ ላይ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ አነሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:21:55 0:00

ባለሥልጣኑ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር በትናንትናው ዕለት ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው እገዳውን ለማንሳት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ፣ ሁለቱ አካላት ባደረጉት ውይይት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

አዲስ ስታንዳርድ በሕወሓት የሚመራውን ኃይል “የመከላከያ ኃይል” ብሎ እውቅና እስከመስጠት በመድረስ የሽብር ቡድኑ አጀንዳ ማራመጃ መድረክ ሆኗል” በሚል ሚዲያውን በጊዜያዊነት ማገዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

እገዳው መነሳቱን በማስመልከት በድረገጹ መግለጫ ያወጣው አዲስ ስታንዳርድ፣ አስቀድሞም እገዳ የተጣለበት ከሕግ አግባብ ውጭ መሆኑን ቢገልጽም ባለስልጣኑ በበኩሉ ከሚዲያው ጋር በተያያዘ ያሉ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ቀጣይ መዘዛቸው ስለማይታወቅ እገዳ አንስቶ ለመወያየት መምረጡን ነው ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የሚዲያ ዐዋጅ በቅርብ ጊዜ የወጣ ከመሆኑ ባለፈ ዐዋጁ በሚደነግገው መሰረት ገና ቦርድ አለመቋቋሙን የገለጹት አቶ መሀመድ፣ ተቋሙ በሽግግር ላይ ከመሆኑ እና ሀገሪቱም ካለችበት ሁኔታ አንጻር በባለስልጣኑ ውሳኔዎች ዙሪያ የሚፈጠሩ ክፍተቶች እንደሚኖሩ አምነው በመነጋገር እየተሸሻሉ እንደሚሄዱ ተናግረዋል፡፡ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቪኦኤ የአዲስ ስታንዳርድን ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ጊዜያዊ እገዳ ከጣለ በኋላ፣ ሁሉም ሚዲያዎች ከሕወሓት ጋር በተያያዘ የትግራይ መከላከያ ኃይል እና የትግራይ ክልል መንግስት የሚል ስያሜ እንዳይጠቀሙ የሚያስጠነቅቅ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

XS
SM
MD
LG