አዲስ አበባ —
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የለገሰችውን 453 ሺ ፀረ ኮቪድ 19 ክትባት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ለጤና ሚንስቴር አስረክበዋል። ልገሳው የተደረገው የጆ ባይደን አስተዳደር ከኮቫክስ ጋር በጥምረት ከለገሰው 25 ሚሊየን የሚጠጋ ክትባት መካከል መሆኑ ነው አምባሳደሯ ገልፀዋል ።
የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ስለክትባቱ የአሜሪካን መንግሥትን ካመሰገኑ በኋላ፤ “ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ባለበት ወቅት የተለገሰ ነው” ብለዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)