አዲስ አበባ —
ኢሰመኮ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በትግራይ ተወላጆች ላይ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር፣ እንግልት እና የንግድ ቤት መዘጋት እንደሚፈጸም መረጃዎች እንደደረሱት መግለጹ ይታወሳል፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ፣ ሕወሓትን በመደገፍ የተጠረጠሩ 325 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል፡፡ በተጠርጣሪዎች ቤት እና የንግድ ድርጅቶች በተደረገ ብርበራ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውንም የገለጹት ኮሚሽነሩ እርምጃው ከብሔር ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል፡፡ የፖሊስ እርምጃ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የጠቆመው ኢሰመኮ፣ በትግራይ ክልልም የሕወሓት ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተፈረጁ ንጹሀን ስለመገደላቸው ማስረጃዎች ደርሰውኛል ማለቱ ይታወሳል፡፡
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)