በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ክልል በ47 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ይካሄዳል ተብሏል


ፎቶ ፋይል፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ
ፎቶ ፋይል፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ

በደቡብ ክልል በ47 የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ እና የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ አስታወቀ። ምርጫው ጳጉሜ 1/2013 የሚደረግ ሲሆን 22 የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝብ ውሳኔ የሚካሄድባቸው ሲሆኑ የቀሩት ደግሞ ምርጫ ቦርድ እንደገና ምርጫው እንዲካሄድባቸው የወሰነባቸው እና በፀጥታ ችግር ምርጫ ያልተደረገባቸው መሆኑም ተገልጿል።

በክልሉ የመጀመሪያው ዙር ሰኔ 14 2013 ዓም ምርጫ ባልተካሄደባቸው በ25 ክልሎች ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ደቡብ እና የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ፍሬው በቀለ ገልጠዋል።

22 የምርጫ ጣቢያዎች የካፋ፥ የሸካ፥ የዳውሮ፥ የቤንች ሸኮ፥ የምዕራብ ኦም ዞኖች እና የኮንታ ልዩ ህዝብ ወረዳ ውሳኔ ህዝብ የሚካሄድባቸው ሲሆኑ የቀሩት ምርጫ ቦርድ እንደገና ምርጫው እንድካሄድባቸው የወሰነባቸው እና በፀጥታ ችግር ምርጫው ያልተደረገባቸው መሆኑም አአስተባባሪው ተናግረዋል።

አሁንም መፈተሽ ያለባቸው ነግሮች እንዳሉ የገለፁት አቶ ፍሬው በፀጥታ ምክንያት ምርጫው ያልተደረገባቸው ቦታዎች ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል አመላካች ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑንም አስታውቀዋል። በመጀመሪያ ዙር ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ ውጤት ለሕዝብ ይፋ መደረጉ እና አሸናፊ ፓርቲ የታወቀበት የምርጫ ውጤት መታወቁ ምርጫው ባልተደረገባቸው አከባቢዎች መራጮች ድምፅ ለመስጠት ተነሳስሽነታቸውን አይቀንስባቸውም የተባሉት አቶ ፍሬው የምርጫው ዋነኛ ዓላማ ወኪሉን መምረጥ ነው ብለዋል። የምርጫ ሂደቱም መደበኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በደቡብ ክልል ባለፈው ሰኔ በ88 ምርጫ ክልሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠርሩ ዜጎች ድምፅ መስጠታቸውን ይታዋሳል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ)

በደቡብ ክልል በ47 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ይካሄዳል ተብሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00


XS
SM
MD
LG