በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዋጃና ጥሙጋ ተፈናቅለው ቆቦ የገቡ ነዋሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና ንብረታቸው እንደተዘረፈ ገለፁ


የአካባቢው ካርታ
የአካባቢው ካርታ

በራያና አካባቢው የከፋ ሰብአዊ ጉዳት ሳይደርስ መንግሥትም ሆነ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲሰጡ ከዋጃና ጥሙጋ አካባቢ በጦርነቱ ምክንያት ሸሽተው የወጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አስታወቁ፡፡ የሰሜን ወሎዎቹ ቆቦና ወልዲያ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተፈናቃዮች እየተቀበሉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ራሱን የትግራይ ኃይል ብሎ የሚጠራው አካል ኮረም፣ አላማጣ፣ ዋጃንና ጥሙጋን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሽዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎ አካባቢያቸውን ለቀው ከሰሜን ወሎዋ ቆቦ እስከ ደሴ በሚገኙ ሮቢት፣ ጎብዮ፣ አራዱም፣ ወልዲያና ሌሎች ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ወሎ በሚገኙት አዲስ ቅኝ፣ ራማ፣ ዞብል፤ ጎለሻ፣ ጀመዶ ማሪያምና ሌሎች የገጠር ከተሞች ተሰደው መሄዳቸውን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ፡፡

ከዋጃ 15 ኪሎ ሜትር ምሽትን ተገን አድርገው በእግራቸው ተጉዘው ሐሙስ ሐምሌ 8/2013 ዓ.ም ቆቦ ከተማ መግባታቸውን አንድ የዕድሜ ባለጸጋ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በኩል ባስተላለፈው መልእክትም ሰራዊቱ ትዕዛዝ በሚሰጠው ጊዜ አስፈላጊውን ርምጃ ሊወስድ የሚያስችለው አቋም ላይ እንደሚገኝ መጥቀሱ ይታወሳል፡፡

(ተፈናቃዮቹ የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ከዋጃና ጥሙጋ ተፈናቅለው ቆቦ የገቡ ነዋሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና ንብረታቸው እንደተዘረፈ ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00


XS
SM
MD
LG