በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጣና ሐይቅ ተሳፍረው ሲጓዙ ከነበሩት ውስጥ የሰባት ሰዎች አስክሬን ተንሳፎ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፡ ጣና ሃይቅ
ፎቶ ፋይል፡ ጣና ሃይቅ

በጣና ሃይቅ ላይ 13 ሰዎችን አሳፍራ በጉዞ ላይ እንዳለች መጥፋቷ ትናንት በተነገረው አነስተኛ ጀልባ አደጋ የሞቱ የሰባት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ።

ከአዲስጌ ደንጌ ቀበሌ ወደ ጎርጎራ ወደብ ባለፈው ዓርብ፤ ሀምሌ 9/2013 ዓ.ም ምሽት ጉዞ ጀምራ የነበረቸው ጀልባ ድንገት መሠወሯ ከታወቀ አንስቶ በሃይቁ ላይ ላለፉት ሁለት ቀናት በጀልባና በዋናተኞች በተካሄደ አድካሚ ፍለጋ የሰባት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ ገልፀዋል።

አስከሬኖቹ ጣና ሀይቅ በሚያዋስናቸው በጎርጎራና አዲስጌ ድንጌ በተባለ የገጠር ቀበሌ መካከል በሀይቁ ላይ በማዕበል ተገፍተው ዛሬ ንጋት ላይ ተንሳፈው መገኘታቸውን ኮማንደር ቸርነት ተናግረዋል። ጀልባዋ ላይ ከተሳፈሩት 13 ሰዎች ሌላ ድንችም ተጭኖ እንደነበረም ታውቋል።

በጣና ሐይቅ ተሳፍረው ሲጓዙ ከነበሩት ውስጥ የሰባት ሰዎች አስክሬን ተንሳፎ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:12 0:00

ተያያዥ ዘገባ

በጣና ሃይቅ ላይ 13 ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መሰወሯ ተሰማ።

(ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በጣና ሃይቅ ላይ 13 ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መሰወሯ ተሰማ።
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:21 0:00


XS
SM
MD
LG