በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሌ ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አቋቋሙ


 የሶማሌ ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አቋቋሙ
የሶማሌ ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አቋቋሙ

የሶማሌ ክልል ተፎካካሪ ፓርቲውፕች የፊታችን ጳጉሜ 1/2013 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ እና ከምርጫ በኋላ በክልሉ ሰላምና ልማት ላይ በጋራ የሚመክሩበት ምክርቤት ማቋቋማቸውን አስታወቁ።

የምዕራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን በመወከል የምክርቤቱ አባል የሆኑት አቶ ሂርሲ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤት ቀጣዩን ምርጫ በሰላም ለማጠናቀቅ ጠቃሚ ነው ይላሉ።

ከዚህ በፊት የምዕራብ ሶማሌ ዶሞክራሲያዊ ፓርቲና የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ ኦብነግ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍህት ኢዜማና ሌሎችም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በእጩዎች ምዝገባና በመራጮች ምዝገባ፣ እንዲሁም በሌሎች ምርጫ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ በተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያቀርቡ ነበር። የምርጫ ቦርድም የእጩዎች ምዝገባን በተመለከተ ቅሬታዎቻቸውን ሰምቶ ማስተካከያ አድርጎላቸው የነበረ ሲሆን የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ የቀረበውን ቅሬታም በምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ ሶማሌ ክልል ሄዶ የመስክ ምልከታ ካካሄደ በኋላ መጀመሪያ ላይ የተወሰኑ ምርጫ ክልሎችን፣ በኋላም ሙሉ በሙሉ የሶማሌ ክልል ምርጫን ወደ ጳጉሜ እንዲተላለፍ ወስኖ ነበር።

አሁን በተቋቋመው የሶማሌ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት የብልጽግና ፓርቲ፣ ኦብነግ፣ ምዕራብ ሶማሌ እና ነጻነትና እኩልነት ፓርቲዎች አባል የሆኑ ሲሆኑ የምዕራብ ሶማሌ በሊቀመንበርነት ምክርቤቱን ለስድስት ወር እንዲመራው ተመርጧል።

የብልጽግና ፓርቲ የምክርቤቱ አባል መሆኑ ቅሬታዎችን ከስር ከስር በውይይት ለመፍታት ጠቃሚ ነው ብለው እንደሚያምኑ የሚናግረሩት አቶ ሂርሲ፤ “ምክርቤቱ ግን ከምርጫ ነክ ጉዳዮች ባሻገር ፓርቲዎቹ ወደፊትም ክልሉን በሚመለከቱ ጉዳዮች በጋራ የሚመክሩበት ይሆናል” ብለዋል።

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የሶማሌ ክልል ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አቋቋሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00


XS
SM
MD
LG