ልክ የዛሬ 10 ዓመት ደቡብ ሱዳን ብዙም ያልቆየ የነጻነት ቀኗን ክብረበዓል በደስታ ማክበር የጀመረችው፡፡ ይሁንና ከሁለት ዓመት በኋላ ሃገሪቱ በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ ጀምረች፡፡ ይሄ ጦርነት እስካሁን ድረስ የ400,000 ሰዎችን ሕይወት በመቅጠፍ እጅግ መጥፎ የሆነ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት 1.6 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በሃገር ውስጥ መፈናቀላቸውን፣ 2.2 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ ደንበር ተሻግረው በስደት እንደሚኖሩ ያሳያል፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት የሕጻናት ፈንድ ዩኒሴፍ 8.3 ሚሊየን ሰዎች እና 4.5 ሚሊየን ሕጻንትን ጨምሮ እጅግ አጣዳፊ የሆነ የሰብዓዊ እርዳታና እና ድጋፍን ይሻሉ ብሏል፡፡