በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሰጡት መግለጫ


ፎቶ ፋይል: የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት 
ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
ፎቶ ፋይል: የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት  ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሰጡት መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00


የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ መቀሌ ውስጥበትግራይ ቴለቭዥን በሰጡት መግለጫ የክልሉን አመራር “ከኅዳር ጀምሮ አጋጥሞት የነበረውን ፈተና ለመግለፅ የሚከብድ ክፉ ጊዜእንደነበር’ ተናግረዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት “ወራሪዎችን ገጥመህ መሻገር ከባድ፣ ድል መቀዳጀትም ጨለማ መስሎ የታየበት ወቅት ነበር” ብለዋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በዚሁ መግለጫቸው “ፋሺስታዊ” ያሉት የአብይ አህመድ ሥርዓት “በተንኮልና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣንላይ ተቆናጥጦ እየገዛ የትግራይ ህዝብ ባካሄደው ህጋዊና ታሪካዊ ምርጫ ለተቋቋመው የትግራይ ብሄራዊ መንግሥት ‘ዕውቅናአልሰጥም፤ አልቀበልም’ ብሎ ለህዝባችን የተመደበ በጀት፣ የሚገባውን ማኅበራዊ አገልግሎትና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዳይደርሰውበጉልበት እና ሌሎች ክፋቶች ከልክሏል።” ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት “አምባገነን” ሲሉ ከጠሯቸው ኢሳያስ አፈወርቂና “ተስፋፊ” ካሏቸው የአማራ ክልል ኃይሎችና “ሌሎች የጥፋትኃይሎች” ካሏቸው ጋር ተባብሮ፣ የህዝብ እና የአገር ሉአላዊነት አሳልፎ ሰጥቷል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ኮንነዋል። “በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ክህደት ፈጽሟል” ሲሉም ከስሰዋል።

‘ወራሪ’ ያሏቸው ኃይሎች ባለፉት ስምንት ወራት “ትግራይን ከዓለም ካርታ ለማጥፋት፣ የትግራይን ህዝብ ከምድር ገጽ ለመሰወር እና ዘሩንለማጥፋት፣ ተከታታይ ወረራዎችን ፈጽመዋል” ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን “እነዚህ ኃይሎች በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንኳን ሊፈጸም ሊታለምእንኳ የማይታሰብ አረመነያዊ ተግባር በመፈጸም የዓለምን ማሕበረሰብ ሳይቀር ያስደነገጠ እኩይ ተግባር ፈጽመዋል’ ብለዋል።

“የትግራይ ህዝብ በረዥም የትጥቅ ትግል፣ በደሙ ና በአጥንቱ ያረጋገጠውን የራስን እድል በራስ የመወሰን እና ራስን የማስተዳደር መብትለመንጠቅ፣ ማንነቱን እና ብሄራዊ ክብሩን ደፍረው፣ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በላቡ ያካበተውኝ ሃብትና ንብረት ዘርፈው፣ አቃጥለው እናአበላሽተው፣ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ እንዲመለስና እንዲደኸይ፣ በረሃብ እና በህመም እንዲያልቅ፣ ከዚህ ክፉ ምኞት ያመለጠ ካለደግሞ ተሰድዶ እንዲበታተን ያልቆፈሩት ጉድጓድ አልነበረም።” ያሉት ዶ/ር ደብረ ጽዮን “ሕዝባዊ ትግል ተገደን የገባንበት እንጂ ፈቅደንእንዳልሆነ ግልጽ ነው” ብለዋል ዶ/ር ደብረጽየን።

XS
SM
MD
LG