በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ ከተማ ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎችና የሚዲያ ሰዎች መታሰራቸው ተገለጸ


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

ለእስራት ከተዳረጉ የትግራይ ተወላጆች መካከል እንደሆነ የገለጸ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወጣት፣ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጠው አስተያየትባለፈው ቅዳሜ ሲቪል በለበሱ ፖሊሶች ተይዞ ከታሰረ በኋላ አመሻሽ ላይ መለቀቁን ተናግሯል፡፡ ማንነቱ እንዲገለጽ ያልፈለገው ይህ ወጣትእርሱና ጓደኞቹ በፖሊስ የተያዙት፣ በኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኝነት ከተፈረጀው ከሕወሓት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተጠርጥረውመሆኑን ገልጿል፡፡ በዛሬው ዕለትም እስራቱ እንደቀጠለም ጠቁሟል፡፡

በተያያዘ መረጃ ጋዜጠኞችም ስለመታሰራቸው ኢሰመኮ እና የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

ታስረዋል የተባሉት ጋዜጠኞች በአውሎ ሚዲያእና ኢትዮ ፎረም የሚሰሩ ሲሆን፣ ከአውሎ ሚዲያ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ባልደረቦችከታሰሩ ሳምንት ቢሆናቸውም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡

ቪኦኤ ከፌዴራል ፖሊስ መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት ለጊዜው ባይሳካም፣ ይሁንና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባአዳነች አቤቤ፣ ዝርዝር ጉዳይ ባያነሱም በአዲስ አበባ ሆነው አሸባሪ ያሉትን ሕወሓትን የሚደግፉ መኖራቸውን ገልጸው እነዚህን አካላትተጠያቂ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ትናንት ተናግረዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)


XS
SM
MD
LG