በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሶቹ የኮቪድ ዝርያዎች እና የክትባት ጥርጣሬ መሃል የተከበረው የዩናይትድ ስቴትስ የነጻነት ቀን


U.S. President Joe Biden delivers remarks at the White House at a celebration of Independence Day in Washington
U.S. President Joe Biden delivers remarks at the White House at a celebration of Independence Day in Washington
አዲሶቹ የኮቪድ ዝርያዎች እና የክትባት ጥርጣሬ መሃል የተከበረው የዩናይትድ ስቴትስ የነጻነት ቀን
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:49 0:00


ዩናይትድ ስቴትስ በትላንትናው ዕለት በተለምዶ ጁላይ ፎር በመባል የሚታወቀውን የነጻነት ቀኗን በደማቁ አክብራለች፡፡ ምንም እንኳን ሃገሪቱ የአዳዲሶቹ የኮቪድ ቫይረስ ዓይነቶች እና የኮቪድ 19 ክትባት ጥርጣሬዎች ስጋት ቢኖርባትም ትላንትና ተክብሮ ከዋለው የአሜሪካ የነጻነት ቀን ጎን ለጎን የፕሬዘዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ኮቪድ 19ን በመዋጋቱ ረገድ ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል፡፡

በአሁን ሰዓት በሃገሪቱ ሶስት በፌደራል ፍቃድ የተሰጣቸው ክትባቶች አሉ፡፡ በዋይት ኋውስ እና በግዛት አስተዳደሮች ከፍተኛ የሆነ የክትባት ቅስቀሳ ዘመቻ ምክንያት የሞት ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን፡፡ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል ሲዲሲ በአሁኑ ወቅት በአማካኝ በዕለት 256 ሞቶች ብቻ እንደሚመዘገቡ አስታውቋል፡፡

የባይደን አስተዳደር 326 ሚሊየን ክትባቶች በላይ መስጠቱን እና 54 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካዊያን የመከተባቸውን ስኬት እያከበሩ ይገኛሉ፡፡ ፕሬዘዳንቱ እስከ የዩናይትድ ስቴትስ የነጻነት ቀን ድረስ 70 በመቶ የሚሆነው አሜሪካው ለመከትብ ያቀዱ ቢሆንም ነገር ግን አሁንም ድረስ የክትባት ጥርጣሬ በመኖሩ አልተሳካም፡፡

በትላንትናው ዕለት ተከብሮ የዋለውን የዩናይትድ ስቴትስ የነጻነት ቀን በአንድነት ተሰባስበው ለማክበር 47 ሚሊየን የሚሆኑ አሜሪካዊያን የተለያዩ መጓጓዣዎችን ይጠቀማሉ ሲል የአሜሪካ የተሽከርካሪዎች ማኅበር ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር፡፡ ይሄ አሃዝ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ40 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል፡፡ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደንም የዘንድሮ በጋ የአውሮፓዊያን በጋ የተለየ ይሆናል ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG