በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች መቅረት ኢትዮጵያ መልስ ሰጠች


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን የታዛቢነት ሚናውን የሰረዘው የኢትዮጵያያን ሉአላዊነት የሚጻረሩ ደህንነቷንም አደጋ ላይ የሚጥሉ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን እንዳይጠቀም በመከልከሉ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ውሳኔ ምዕራባዊያኑ በሉአላዊ የአፍሪካ አገራት ላይ የሚያራምዱት ያልተገደበ ጣልቃ ገብነታቸው ማሳያ ነው ሲሉ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተችተዋል፡፡

ትናንት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች በሰጡት መገለጫ እንዳስታወቁት የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዘቢ ቡድን በታዛቢነት አገር ውስጥ ለመግባት ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጻረሩ፣ ነጻነቷን የሚዳፈሩ፣ ሰላሟን አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው፡፡

ታዛቢ ቡድኑ ወደ አገር ውስጥ ለመግባት የነበረውን ውሳኔ የሰረዘው እንደ አምባሳደሩ መሰረታዊ ባሏቸው ሁለት ጭብጦች ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ባለመፈጠሩ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ለአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች መቅረት ኢትዮጵያ መልስ ሰጠች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:13 0:00


XS
SM
MD
LG