በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች አይልክም


የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ጆሲፕ ቦሬል
የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ጆሲፕ ቦሬል

አስፈላጊውን ሁሉ ጥረቶች ያደረግን ቢሆንም መጪውን የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲታዘቡ ለሚላኩ ልዑካን መሟላት ያለባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልቻልንም ያሉት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ጆሲፕ ቦሬል የጠየቅናቸው ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ታዛቢ ቡድኑን ጉዞ ሰርዘናል ሲሉ አስታወቁ።

የአውሮፓ ህብረት ለዲሞክራሲ ግንባታ በሚሰጠው ድጋፍ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ተዓማኒነት መሰረታዊ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፣ ለማናቸውም የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሟላት የሚያስፈገውን ጉዳይ ለሙዋላት ፈቃደኛ አለመሆናቸው አሳዝኖናል ብሏል።

የምርጫ ታዛቢው ቡድን ነጻነት እንዲረጋገጥና እና ታዛቢ ቡድኑ የኮሙኔኬሽን (የመገናኛ) መሳሪያዎችን ይዞ እንዲገባ መጠየቁን ገልጾ ይህ በተለይ ካሉት የጸጥታ ድባብ ተግዳሮቶች አንጻር

ለህብረቱ ታዛቢዎች ደህንነት መሟላት ያለበት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አመልክቷል።

የሁኔታው አንድምታ የመራጭ ምዝገባውን ጨምሮ፣ በምርጫው ዝግጅትም ላይም ጭምር የሚታይ እንደሆነ ነው የአውሮፓ ህብረት መግለጫው ያተተው።

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲን ለመቀዳጀት የሚያደርገውን ታላቅ ጉዞ እጅግ ጉልህ ከሆኑት የድጋፉ መገለጫዎች አንዱ በሆነው በዚህ ተልዕኮ ለማሳየት የሚያስፈልጉት ጉዳዮች እንደሚሙሉ ማረጋገጫ አለማግኘቱ አሳዝኖናል ሲል መግለጫው አስታውቋል። የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያውን በሙሉ በህጋዊው የፖለቲካና የሲቪል መብቶቻቸው መጠቀማቸውን ለማረጋገጥ ይበልጡን ጥረት እንዲያደርጉ እናሳስባለን ሲል አክሏል።

ቪኦኤ የመጪውን ምርጫ ዝግጅት ሂደት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬቴሪያት ቢል ለኔ ስዩም ቢሮ ያገኘው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫዎቹ በሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ለማከናወን ባለው ቁርጠኝነት ጸንቶ እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

በማስከተልም ለዓለም አቀፍ ታዛቢ ቡድኖችም ባለው አቅም አስቻይ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፍላጎቱን ሲገልጽ ቆይቷል።

አሁንም ምርጫውን ለመታዘብ የሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችን በደስታ እንቀበላለን ያሉት ቢል ለኔ ስዩም የሆነ ሆኖ የምርጫውን ቅቡልነት በዋናነት የሚያረገግጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፤ ለሰላምና ለዲሞክራሲ በቁርጠኝነት እንዲቆም የሚጠየቀውም ህዝቡ ነው ብለዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሁሉ የዲሞክራሲ መብታቸውን ተጠቅመው ድምጻቸውን ለመስጠት መመዝገባቸውን እንዲቀጥሉ እናበረታታለን ያለው መግለጫው ማህበረሰቦቻቸውንም በንቃት እንዲጠብቁ እናሳስባለን ብሏል።

XS
SM
MD
LG