በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴነተር ኩንስ ጠ/ሚ ዐቢይን አነጋግረው ተመለሱ


ፎቶ ፋይል፦ ሴነተር ክሪስ ኩንስ
ፎቶ ፋይል፦ ሴነተር ክሪስ ኩንስ

በትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ እንዲነጋገሩ የዩናይትድ ስትትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ አዲስ አበባ የላኳቸው ሴናተር ክሪስ ኩንስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መገናኘታቸው ታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለአሜሪካ ድምጽ እንዳሉት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር እና የሕዳሴው ግድብ ድርድር ጉዳዮች በውይይቱ ከተነሱት መካከል ናቸው።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለም ከሴናተር ኩንስ ጋር በትግራይ ክልል ባለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ መወያየታችውን በተመሳሳይ ለአሜሪካ ድምጽ አስረድተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ሴነተር ኩንስ ጠ/ሚ ዐቢይን አነጋግረው ተመለሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:48 0:00


XS
SM
MD
LG