በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ሴነተር ኩንስን ወደ ኢትዮጵያ ላኩ


ሴነተር ክሪስ ኩንስ እኤአ ነሀሴ 13/ 2019 በዓለም ካሉ ትላልቅ የስደተኛ ጣቢያዎች አንዱ የሆነውን የዩጋንዳውን የቢዲ ቢዲ መጠለያን በጎበኙበት ወቅት
ሴነተር ክሪስ ኩንስ እኤአ ነሀሴ 13/ 2019 በዓለም ካሉ ትላልቅ የስደተኛ ጣቢያዎች አንዱ የሆነውን የዩጋንዳውን የቢዲ ቢዲ መጠለያን በጎበኙበት ወቅት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በጣም አሳስቧቸዋል በተባለውና፣ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የብዙ ሺ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ በተነገረለት፣ ቀውስ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ተገናኝተው እንዲመክሩ፣ ዴሞክራቱን የምክር ቤቱ ህግ አስፈጻሚ ክሪስ ኩንስን ወደ ኢትዮጵያ መላካቸው ተነግሯል፡፡

ዋሽንግተንም እንዲሁ በክልሉ ተከስቷል ለተባለው ሰብአዊ ቀውስ ወደ 52 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ እርዳታ እንደሚሰጥ በማስታወቅ በክልሉ እየተደረገ ነው የተባለው በደልና ጥቃት እንዲቆምና፣ የሰአብዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙትም ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊነከንም በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ የኤርትራ ኃይሎች ክልሉን ለቀው በአስቸኳይ እንዲወጡና የኢትዮጵያ መንግሥትም በትግራይ የሚያደርገውን የክልል ኃይሎች ስምሪት እንዲያቆም፣ የሰአብአዊ እርዳታዎችን ማድረግ የሚቻልበትን መንገዶች ይበልጥ እንዲያመቻች አሳስበዋል፡፡ ብሊንከን በመግለጫቸው

“የፖለቲካ መፍትሄ ካልተሰጠው ሰብአዊ ቀውስ ይበልጥ እየተባባሰ ይሄዳል” ብለዋል፡፡

በትግራይ የህወሃት ኃይሎች እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል በሚደረገው ጦርነት፣ ብዙ ሺ ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን፣ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም እንዲፈናቀሉ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ የተፈጠሩ ሰብአዊ ጥሰቶች ያሳሰበው መሆኑን ሲገልጽ፣ አንተኒ ብሊንከንም፣ “የአንድን አካባቢ ሰዎች ከአንዳንድ ቦታዎች ለይቶ የማጥፋት ድርጊት ተፈጽሟል” እስከማለት ሄደዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የብሊንከንን አስተያየት

“መሠረተ ቢስና የቅጥፈት ውንጀላ ነው” ብሎታል፡፡ እኤአ ባለፈው ማርች 13 ባወጣው መግለጫም

“በትግራይ ክልል ዋናው የህግ ማስከበር ዘመቻ ሲካሄድም ሆነ በማብቂያው ሂደት ላይ ፣ ሆን ተብሎ የተወሰኑት ሰዎች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጽዳት ነው ተብሎ በየትኛውም መመዘኛ ሊታወቅ ወይም ሊገለጽ የሚችል ነገር የለም፡፡” በማለት “የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲህ ያሉ ክሶችን አጥብቆ ይቃወማል” ብሏል፡፡

የባይደን የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ባወጡት መግለጫ ሴነተር ኩንስ የባይደን የረጀም ጊዜ ወዳጅ ናቸው ብለዋል፡፡

ባይደን ሴነተር ኩንስን ወደ ኢትዮጵያ ላኩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:29 0:00


የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ከሆነችው ክፍለ ግዛት ደለዌር የተመረጡ መሆናቸውንም ገልጸው፣ በኢትዮጵያው ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረትም ጋር በጉዳዩ እንደሚመክሩ አስታውቀዋል፡፡

ኩንስ “ባይደን በአፍሪካ ቀንድ ያለው አለመረጋጋትና በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስም ያሳስባቸው መሆኑን ለአፍሪካ መሪዎች ያስረዳሉ” ብለዋል፡፡

በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት፣ በአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ የጤና ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ ውስጥ ያገለገሉት ሴነተር ኩንስ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ተገናኝተው በፕሬዚዳንት ባይደንን ስጋት ላይ እንደሚነጋገሩ ተናግረዋል፡፡

ጉዞአቸውን አስመልክተው ባወጡት መግለጫ “እየተባባሰ የመጣው ለአፍሪካ ቀንድ ችግር ሊፈጥር ይችላል የተባለው የትግራይ ክልል ሁኔታ ዩናይትድ ስቴትስን በእጅጉ ያሳስባታል” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ጦር ባላፈው ህዳር ወር ውስጥ፣ በኤርትራ አዋሳኝ በሚገኙ የፌደራሉ መንግሥት ኃይሎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽመዋል ያላቸውን የሕወሃት ኃይሎችን ከመቀሌ አስወግዷል፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነቱ አብቅቷል ቢልም፣ አንዳንድ የተኩስ ልውውጦች በተለያዩ አካባቢዎች መኖራቸውንግንአስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች፣ በርካታ የዓይን ምስክሮችና አንድ የኢትዮጵያ ጀኔራል፣ በክልሉ የኤርትራ ኃይሎች በውጊያው መሳተፋቸውን ቢገልጹም፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ግን አስተባብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG